የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ስልጤ ልማት ማህበርን...

Read More

ስልጤ ልማት ማህበር አባላት ፣ ደጋፊዎችና አጋሮች የቀረበ ጥሪ !! እንደሚታወቀው የስልጤ ልማት ማህበር የስልጤን ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚል ጥር 25/ 1994 የተመሰረተ መንግስታዊ ያልሆነ ልማት ማህበር ነው ፡፡ የስልጤ ልማት ማህበር ከልማት ድርጅቶች ሁሉ ልዩ የሚያደርገው ከልማት ጋር ብቻ የሚተሳሰር ልማት ማህበር ብቻ ሳይሆን ከስልጤ ህዝብ ማንነት ጋር የተያየዘ ልማት ማህበር ነው ፡፡ የስልጤ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደርና የማንነት ህጋዊ እውቅና እንዲሰጥ ለአስር ዓመታ ት ተከታታይ ዓመታት ትግል በማድረግ በ1993 በህዝበ ውሳኔ ድምፅ ውሳኔ ማግኘቱን ተከትሎ የስልጤ ዞን የአስተዳደር መዋቅርንና የስጤ ልማት ማህበርን መመስረት ተቻለ ፡፡ ለዚህ ነው የስልጤ ልማት ማህበር ታሪካዊ አመሰራረት ከልማት ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም ከማንነቱም ጋር የተቆራኘ ልማት ማህበር ነው ፡፡ ስለሆነም ልማት ማህበሩን ከአባላትና ከደጋፊዎቹ ጋር በማስተሳሰርና በማቀራረብ ፣ ለመደጋገፍ ፣ ንቅናቄ ለማድረግ ፣ አባሉ ስለ ልማት ማህበሩ መረጃ ለማግኘትና የአባላትን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ፣ በልማት ማህበሩ የሚሰሩ ስራዎችን ለአባሉ ተደራሽ ለማድረግ ሚዲያ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይታወቃል ፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ልማት ማህበሩ ከፌስቡክ ገፅ ባሻገር ፣በቲክ ቶክ ፣ በዩቱብ ፣ በስልጤ ኤፍ ኤምና በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለአባላቱ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ መሆናችንን እየገለፅን በመላው ዓለም የምትገኙ የልማት ማህበሩ አባላት ፣ደጋፊዎችና አጋሮች የልማት ማህበራችን የሚዲያ አማራጮች ተከታይ እንዲሆኑና የፌስቡክ ገፃችን ለድጅታል ተከታይ አባሎቻችን ተደራሽ እንዲሆን የተከታዮቻችን አባላት እንድታሳድጉ በስልጤ ልማት ማህበር ስም ተጠየቋል ፡፡ አቦት ማልዳዶነዋ ኢንደቸነ ሌበልነት ጃዴ ባሎ ጭም ጭም አሱናን !! አኩም በሰ አለነቢ አዝጋግ የጠቀለ ጭም ጭም ለበሎት ለፌስቡክ ወሻሾ ላጃጂጅነ !!

 

Read More

በትምህርቱ ዘርፍ ጠንክረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሳያ ነው ፦ አቶ ዘይኔ ቢልካ! ይህንንም ልምድ ወደ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማስፋት እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ተናግራዋል፡፡ የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ለውጤቱ መብቃት አስተዋጽኦ ለደረጉ መምህራን የሽልማትና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግብር በወራቤ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በዚህ ወቅት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንደገለጹ...

Read More